የመኖሪያ ቤት ገበያ
አብዛኛው የስዊስ ነዋሪዎች የሚኖሩት በኪራይ አፓርታማ ነው። የግንባታ መሬት መገንባት እጥረት ስላለ በተለይ በከተሞች እና በመሐል ከተማ ውስጥ ብዙ ነጻ የሆኑ አፓርታማዎች አይገኙም። የኪራይ ዋጋ ከፍተኛ ነው። ከገቢዎ ውስጥ አንድ አራተኛውን ለቤት ኪራይ ማውጣት ያልተለመደ ነገር አይደለም። ከመሐል ከተማ ውጭ አፓርታማ መፈለግ ያዋጣል። በቤቶች ህብረት ስራ ማህበራት ውስጥ ያለው ኪራይ አብዛኛውን ጊዜ ዝቅተኛ ነው። የቤት ኪራይ ውል ከመፈጸሙ በፊት ለዚሁ ዓላማ የኅብረት ሥራ ማህበሩ የአባልነት ድርሻ (Anteilsscheine) መጀመሪያ ላይ መግዛት አለባቸው። የገቢ መጠናቸው ትንሽ የሆኑ ቤተሰቦች እንደ ሁኔታው መስፈርቱን ካሟሉ የቤተሰብ የኪራይ የድጋፍ ድጎማ (Familienmietzinsbeiträge). ማመልከት ይችላሉ።