ለመወሃሃድ የሚረዱ አቅርቦቶች

በት/ቤት፣ በሙያ ስልጠና እና በስራ ቦታ ከሁሉም በተሻለ ሁኔታ መወሃሃድ ይችላሉ። ምናልባትም ስራ አይኖሮት ይሆናል ወይም የሙያ ስልጠና ላይ ላይሆኑ ይችላሉ። እንዲሁም ትምህርት ላይ ላይሆኑ ይችላሉ። ይህ ከሆነ ለመወሃሃድ የሚያግዙ የተለያዩ አቅርቦቶችን መጠቀም ይችላሉ።

ልዩ አቅርቦቶች

በተለይ አዲስ ወደ ባዝል ለመኖር ለመጡ ሰዎች የሚሆኑ ብዙ አቅርቦቶች አሉ። ለምሳሌ ይህል፣ በጠርጴዛ ዙርያ መነጋገር፣ የእረፍት ግዜ አቅርቦቶች፣ ሴሚናሮች ወይም ኮርሶች ይጠቀሳሉ። እነዚህ አቅርቦቶች ቶሎ እንዲለምዱ እና አዲስ ሰዎችን መተዋወቅ እንዲችሉ እንዲረዳዎት የታሰቡ ናቸው። የ"GGG Migration" ምክር አገልግሎት ጽ/ቤት ስላሉት አቅርቦቶች መረጃ ይሰጣል።

በካንቶኑና በመኖሪያ ሰፈርዎ አዲስ ነዋሪዎችን ለመቀበል ዝግጅቶችን ያካሂዳሉ። እዛም ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎችን እና ለመጀመሪያ ያክል የሚሆን አጠቃላይ ዕይታ እንዲኖሮት ያስችሎታል።

ማህበራት

ብዙ ስዊዘርላንዳውያን የማህበር አባላት ናቸው። የተለያየ ፍላጎት ላላቸው እንደፍላጎታቸው የተለያዩ ማህበራት (Verein) አሉ። ለምሳሌ ያህል የስፖርት ክለብ ማህበራት ወይም ባህላዊ ማህበራት፣ የአንድ ማህበር አባል መሆን አዲስ ሰዎችን ለመተዋወቅ ያስችላል። ብዙዎቹ ማህበራት ለሁሉም ሰው ክፍት ናቸው።

የስደተኞች ድርጅቶች

የስደተኞችም ማህበራት አሉ። የማበራቱ አባላት አብዛኛውን ግዜ ተመሳሳይ ቋንቋ ይናገራሉ፣ ከአንድ አገር ነው የመጡት ወይም ተመሳሳይ ሃይማኖት አላቸው። እነዚህ ማህበራት ለስዊዘርላንድ እና ለባዝል ከተማ ካንቶን አዲስ መጤዎች ብዙውን ግዜ አቅርቦት አላቸው። የመዋሃድ ሂደቱ እንዲሳካ አስተዋጽኦና ድጋፍ ያደርጋሉ።

አቅርቦቶች ለወጣቶች

ወጣቶች በትርፍ ጊዚያቸው ያሉትን አቅርቦቶች ቢጠቀሙ፣ ከሌሎች ከእድሜያቸው ጋር ተመጣጣኝ ከሆኑ ወጣቶች ጋር እንዲተዋወቁ ያስችላቸዋል። ፕሮጀክት ላይ መሳተፍና የራሳቸውን የግላቸውን ሃሳብ ማቅረብ ይችላሉ። ባለሙያዎች ወጣቶችን የሙያ ድጋፍ እንዲሁም አብረዋቸው በመሆን ሙያዊ ክትትል ያደርጉላቸዋል (Jugendarbeit)። በመሰረቱ አቅርቦቶቹ ከክፍያ ነጻ ናቸው።

የአካባቢ የመገናኛ ማዕከላት

የአካባቢ የመገናኛ ማዕከላት (Quartiertreffpunkte) ለሁሉም ሰው ክፍት ናቸው። ለቤተሰቦች፣ ለአረጋውያን እና ትንሽ ጀርመንኛ ለሚናገሩ ሰዎች ጭምር የሚሆኑ አቅርቦቶች አላቸው። አንዳንድ የመገናኛ መዝናኛ ማዕከላት የቤተሰብ ማዕከሎች ናቸው። የአካባቢ የመገናኛ ማዕከላት የዕለት ተዕለት ሕይወትን በሚመለከት ምክርና ድጋፍ ይሰጣሉ። በመገናኛ መዝናኛ ማዕከላት ቤተሰባዊ በዓሎችን እና ሌላ ልዩ ዝግጅቶች ለማክበር ክፍሎችን መከራየት ይቻላል።