ውህደት

በBasel-Stadt ካንቶን የሚኖሩ ከሆነ፣ እንደነዋሪ መጠን የተወሰነ መብት አለዎት። ጾታዎ ወንድ ይሁን ሴት ቢሆን፣ ከየትም አገር ይምጡ፣ የፈለጉትን ቋንቋ ይናገሩ፣ በየትኛውም ሃይማኖት ይመኑ ወይም የሆነ ዓይነት ስንክልና ይኑሮት፣ ምንም ልዩነትና ለውጥ አያመጣም። የአገሪቱን ሕግ ግን የማክበር ግዴታ አለብዎት። ከዚህ በተጨማሪም በኢኮኖሚ ራስዎን መቻል እንዲሁም ጀርመንኛ መማር አለብዎት። ይህንን በሚመለከት ከዚህ በታች በቂ መረጃ ያገኛሉ።

ጠቃሚ መሰረታዊ ሕጎች

ስዊዘርላንድ ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ፣ የፌደራሉን ሕገ መንግስትና እንዲሁም ሌሎች ሕጎችን የግድ ማክበር አለብዎት። ይህ ማለት ለምሳሌ ያህል፣ ሁሉም ሰው በእኩልነት መስተናገድ አለበት፣ ማንም ሰው መገለል የለበትም። የባዝል ነዋሪ ከሆኑ ጀርመንኛ መማር ይገባዎታል። ከዛ በተጨማሪም በኢኮኖሚ ራስህዎን መቻል አለብዎት።

በመግባባት ተዋህዶ መኖር የሚቻለው፣ ሁሉም ሰው ድርሻውን አስተዋጽኦ ሲያደርግ ነው። የባዝል ህዝብ በወገኑ ለእናንተ ክፍት መሆን አለበት። ህዝቡ መረጃ በመስጠት መተባበርና ድጋፍ ማድረግ አለበት።

የግለሰብ ሃላፊነት

ወደ ባዝል ከተማ አዲስ ነው የመጡት? በኢኮኖሚ፣ በሶሻል እና በባህላዊ ህይወት ውስጥ ተካፋይ እንዲሆኑ ፌደራሉ፣ ካንቶኖች እና ኮምዩኖች ተገቢው ዕድል የመስጠትና የማመቻቸት ሃላፊነት አለባቸው። ሆኖም ግን እርስዎ በአግባቡ ለመወሃሃድ ጥረት ማድረግ አለብዎት። ከርስዎ የምንጠብቀው፣ በአግባቡ ለመወሃሃድ እንዲያግዝ በማለት የተዘጋጁትን የውህደት አቅርቦቶች በትክክል እንዲጠቀሙበት ነው።

በማህበራዊ ህይወት ውስጥ መሳተፍ

በዚህ መልክ በአግባቡ መዋሃድ ይችላሉ፣ በማህበራት ውስጥ በጣም መልካም ሰዎችን መተዋወቅ ይችላሉ። ወይም በመኖሪያዎ አካባቢ በሚዘጋጁ ማህበራዊ በዓላቶችና ዝግጅቶች መሳተፍ ይረዳል። ምናልባት በመጀመሪያ ግዜ ከባድ ሊሆን ይችላል። አንዳንድ ሰዎች ከሌላ አገር መጤ ከሆኑ ሰዎች ጋር ለመግባባት ክፍት አይደሉም። ይሁን እንጂ ብዙ ሰዎች ለመላመድ ግዜ ያስፈልጋቸዋል፣ ቀስ በቀስ ግን ፈታ እያሉ ይመጣሉ። ስለዚህ በቀላሉ ተስፋ አይቁረጡ።

መረጃዎች / ድጋፍ

ወደ ባዝል አዲስ ነው የመጡት፣ ስለሆነም ድጋፍና መረጃ ያስፈልግዎታል? በ Basel-Stadt መረጃ ማግኘትና መጠየቅ የሚችሉባቸው የተለያዩ ቦታዎችን ማግኘት ይችላሉ። በ Basel-Stadt ካንቶን አስተዳደር ጽ/ቤቶች እና በሚኖሩበት ኮምዩን ጽ/ቤት መረጃዎች ማግኘት ይችላሉ። ይሁን እንጂ ለስደተኞች የተለየ የመረጃ መስጫ አገልግሎት ቢሮዎች አሉ።

በስዊዘርላንድ ስላለው ሕይወት እና ስለ ሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች መረጃ የሚያገኙበት ቦታ፣

  • GGG Migration

የጥገኝነት ሕግ እንዲሁም ስለ የውጭ ዜጋዎች ሕግ በሚመለከት መረጃ የሚያገኙበት ቦታ፣

  • Beratungsstelle für Asylsuchende BAS
  • Freiplatzaktion

የጀርመንኛ ቋናቋ መናገር አይችሉም? ካልቻሉ ሊያስተረጉምሎት የሚችል ሰው ይዘው መሄድ ይችላሉ። አለበለዚያም ተርጓሚ እንዲመደብሎት መጠየቅ ይችላሉ።