ጀርመንኛ ቋንቋ መማር

በጀርመን ኮርስ ጀርመንኛ ቋንቋ በደንብ መማር ትችላለህ። ብዙ የተለያዩ ዓይነት የጀርመንኛ ቋንቋ ኮርሶች አሉ።

አቅርቦቶች

ብዙ የተለያዩ ዓይነት የጀርመንኛ ቋንቋ ኮርሶች አሉ። ለምሳሌ፣

  • ትናንሽ ልጆች ካለዎት የህጻናት እንክብካቤ ያለበት ኮርስ ይመዝገቡ።
  • ምናልባት የላቲን /የእንግሊዝኛ/ ፊደል ዕውቀት ከሌለዎት ወይም ማንበብና መጻፍ ችግር ካለብዎት፣ የማይምነት/የፊደል ትምህርት/ ኮርስ (Alphabetisierungskurs) ይመዝገቡ።.

ምን ዓይነት ኮርሶች እንዳሉ ለማወቅና እና ኮርሶቹ ምን ያህል እንደሚያስክፍሉ መረጃ ለማግኘት እዚህ ይጠይቁ።

  • የጎልማሶች ትምህርት ሙያዊ ቢሮ (Fachstelle Erwachsenenbildung)
  • GGG Migration

የቋንቋ ችሎታ ደረጃ

አንድ ሰው ምን ያህል ጀርመንኛ መናገር እንደሚችል (Gemeinsamen Europäischen Referenzrahmen) „በጋራ የአውሮፓ የማጣቀሻ ማዕቀፍ“ መገምገም ይቻላል። ይህም በምህጻረ ቃል GER ተብሎ ይጠራል። GER የቋንቋ ደረጃ መገምገሚያ መለኪያ ነው። 6 ደረጃዎችም አሉት። እነሱም፣ ኤ1፣ ኤ2፣ ቤ1፣ ቤ2፣ ሴ1 እና ሴ2.ናቸው። ኤ1 ወይም ኤ2.ደረጃ ላይ ከደረሱ፣ መሰረታዊ የጀርመን የቋንቋ ዕውቀት አለዎት ማለት ነው። ሴ1 እና ሴ2.ደረጃ ላይ ከደረሱ፣ ከፍ ያለ የቋንቋ ደረጃ ላይ ደርሰዋል ማለት ነው።

  • ስዊዘርላንድ ውስጥ ተቀባይነት ያለው የሙያ ስልጠና ማድረግ ከፈለጉ፣ ቤ1 ወይም ቤ2 የቋንቋ ደረጃ ያስፈልጋል።
  • ዩንቨርስቲ መማር ከፈለጉ፣ ሴ1 ወይም ሴ2.የቋንቋ ደረጃ ያስፈልጋል።

ፋይናንስ ማድረግ

ለባዝል ከተማ አዲስ ነህ፣ እንዲሁም „የመቆያ ፍቃድ B“ Aufenthaltsbewilligung (B) ተሰጥቶታል? ተሰጥቶት ከሆነ በተጨማሪ የጀርመን ኮርስ ለመመዝገብ የሚያስችል Gutschein ኩፖን ይሰጥዎታል። ይህ ኩፖን 80 የትምህርት ጊዜዎችን በነጻ እንድትማር ያስችልሃል። በካንቶኑ ዕውቅና በተሰጠው የቋንቋ ት/ቤት ኩፖኑን በመስጠት መመዝገብ ይቻላል። ይህ ኩፖን ከገቡበት ግዜ ጀምሮ እስከ 12 ወራት ድረስ ያገለግላል።

ከዚያ በኋላ ተጨማሪ የጀርመንኛ ኮርስ መማር ይፈልጋሉ? መቀጠል ከፈለጉ ለቀጣዩ ትምህርት ክፍያ መክፈል አለብዎት። የኮርሶቹ የክፍያ ዋጋ የተለያየ ነው። በተቻለ መጠን ዋጋ ቢያነጻጽሩ ይመረጣል። የKanton Basel-Stadt ለአንዳንድ ኮርሶች የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋል። በዚህም ምክንያት ለነዚህ ኮርሶች አነስተኛ ገንዘብ ይከፍላሉ።