መሰረታዊ መርሆዎች
የማህበራዊ ዋስትና የሚሸፈነው በስዊዘርላንድ ነዋሪዎች ነው። የአብሮነት መርህ ተግባራዊ ይሆናል፡ አብዛኛው ህዝብ መዋጮ የሚከፍል ሲሆን ግለሰቦች እና የተወሰኑ የህብረተሰቡ አባላቶች ደግሞ ድጋፍ/ድጎማ/ ያገኛሉ። ማህበራዊ ዋስትና በአብዛኛው ግዴታ ነው። ሆኖም ግን መዋጮዎቹ በቀጥታ ከሠራተኞች ደመወዝ ይቀነሳል። ነገር ግን ቀጣሪዎች፣ በግል ሥራ የሚተዳደሩ ሰዎች እና ስራ የሌላቸው የገንዘብ መዋጮ ያደርጋሉ።