ማህበራዊ እርዳታ
ማህበራዊ እርዳታ (Sozialhilfe) በስዊዘርላንድ ውስጥ የተቸገሩ ሰዎችን ሁሉ ይደግፋል። አነስተኛ የኑሮ ወጪዎች ይሸፍናል። ከገንዘብ እርዳታ በተጨማሪ የምክር አገልግሎት ይሰጣል። ዓላማው ሰዎች በተቻለ በፍጥነት እንደገና በኢኮኖሚ ራሳቸውን እንዲችሉ ነው። አንድ ሰው ኑሮውን ለመደገፍ በቂ ሌላ የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኝ ከሆነ፣ የማህበራዊ ዋስትና ክፍያ አይከፈለውም። ለምሳሌ ያህል፣ እንደ የሥራ አጥነት የድጎማ ገንዘብ፣ ጡረታ፣ ደመወዝ ወይም ከዘመዶች ድጋፍን ይጨምራል። ዕዳ ቢኖርም እንኳን አይከፍልም። እንደገና በቂ የፋይናንስ ምንጭ ገቢ ሲኖርዎት፣ ገንዘቡ መመለስ አለበት። ይህ ማህበራዊ እርዳታ የሚሸፈነው በግብር ከፋዮች ነው።