የሥራ አጥነት ኢንሹራንስ
የስራ አጥነት መድን ኢንሹራንስ (ALV) የመንግስት ተቋም ሲሆን ለሁሉም ሰራተኞች አባል መሆን ግዴታ ነው። ወርሃዊ መዋጮ በቀጥታ ከደመወዝ ይቆረጣል፣ አሠሪው ግማሹን ይከፍላል። በግል ስራ የሚተዳደሩ ለሥራ አጥነት ዋስትና መድን አባል መሆን አይችሉም። ሥራ አጥ የሆነ ማንኛውም ሰው ከሥራ አጥ ኢንሹራንስ ፈንድ ወርሃዊ የደመወዝ ምትክ (የሥራ አጥ ድጎማ ክፍያ፣ Arbeitslosengeld) ይቀበላል። መቼ እና ምን ያህል የሥራ አጥነት ክፍያ/ድጎማ/ ማግኘት እንደሚቻል፣ በብዙ በተለያዩ መስፈርቶች ይወሰናል። ለምሳሌ ያህል ጊዜ ስራ እንደሰራና ወይም ስራ አጥ የሆነበት ምክንያት ይወስነዋል።