የአረጋውያን እና የመበለቶች የመድን ኢንሹራንስ (1 ኛ ምሰሶ፣ 1. Säule)
የአረጋውያን እና የመበለቶች የመድን ኢንሹራንስ (AHV) የመንግስት ተቋም ነው። አብዛኛው አዋቂዎች ከዚህ ለመጠቀም መዋጮ መክፈል አለባቸው። መዋጮዎቹ በቀጥታ ከሠራተኞች ከወርሃዊ ደመወዛቸው ይቀነሳል። አሠሪው ግማሹን ይከፍላል። በግል ሥራ የሚተዳደሩ ሰዎች ወይም ሥራ የሌላቸው ሰዎች መዋጮውን እንዴት መክፈል እንዳለባቸው ከካሳ ቢሮ (Ausgleichskasse) መጠየቅ አለባቸው። AHV ለጡረተኞች ወርሃዊ ጡረታ ይከፍላል። የጡረታ መጠኑ እስካሁን በተከፈለው መዋጮ ብዛት ላይ የተመሰረተ ነው። ሆኖም ግን፣ AHV በተጨማሪም የሟቹን የትዳር ጓደኛ እና ልጆች በሞት ጊዜ (የመበለት እና ወላጅ አልባ ጡረታ) ይደግፋል። ሁሉም ሰው የግል የኢንሹራንስ ልዩ ቁጥሩን የያዘ የAHV ካርድ ይቀበላል።