ተከታታይ ትምህርት / ኃላፊነቶች
ስዊዘርላንድ ውስጥ ተከታታይ የሆኑ ሶስት የትምህርት ደረጃዎች አሉ።
- የግዴታ ትምህርት ቤት (Volksschule: Kindergarten, Primarschule und Sekundarstufe I)
- መሰረታዊ የሙያ ትምህርት ወይም መካከለኛ ትምህርት (Sekundarstufe II)
- ከፍተኛ የሙያ ዩንቨርስቲ / መደበኛ ዩንቨርስቲዎች እና ከፍተኛ የሙያ ትምህርት ቤቶች (Tertiärstufe)
መንግስታዊ /ህዝባዊ/ ማዕከላት ለሙያ ትምህርት በበላይነት ይቆጣጠራሉ። በፌደሬሽን፣ በካንቶን እና በኮምዩኖች ደረጃ ተግባርና ሃላፊነቱን ይጋራሉ። በየካንቶኖቹ የተለያየ ዓይነት ትምህርት ቤቶች እና የትምህርት ስርዓቶች ያሉት በዚህ ምክንያት ነው።