የወሊድ ምዝገባ
የወለዷቸውን ልጆች ሁሉንም በነዋሪዎች መመዝገቢያ ጽሕፈት ቤት (Zivilstandsamt) ማስመዝገብ አለብዎት። ማሳሰቢያ: ልጅዎ በተወለደበት ቦታ ባለው የነዋሪዎች መመዝገቢያ ጽሕፈት ቤት ሄደው ልጅዎን ማስመዝገብ አለብዎት። ምናልባትም ወደ መኖሪያዎ ወዳለው የነዋሪዎች መመዝገቢያ ጽሕፈት ቤት ቢሮ መሄድ ላያስፈልጎት ይሆናል።
ልጅዎ ሆስፒታል ከሆነ የተወለደው:
ሆስፒታሉ ሰነዱን ወደ የነዋሪዎች መመዝገቢያ ጽሕፈት ቤት በቀጣይነት ይልከዋል። ይህም ማለት እርስዎ ምንም ማድረግ አይጠበቅብዎትም።
ልጅዎ ሆስፒታል ካልሆነ የተወለደው:
ልጅዎ የተወለደው ምናልባት ቤት ውስጥ ወይም ሌላ ቦታ ሊሆን ይችላል፣ ይህ ከሆነ ልጅዎን በአካል የነዋሪዎች መመዝገቢያ ጽሕፈት ቤት ያስመዝግቡት። ለማስመዝገብ 3 ቀን ይሰጥዎታል። የነዋሪዎች መመዝገቢያ ጽሕፈት ቤቱ ለምዝገባው ማቅረብ ያለብዎትን ሰነዶች ይነግርዎታል።
ማወቅ ያለብዎት መረጃ፣
ስዊዘርላንድ የተወለደ ልጅ ስዊዘርላንድ ስለተወለደ ብቻ ዜጋ አይሆንም። ወዲያውኑ የስዊዘርላንድ ዜግነት አይሰጠውም።