ስዊዘርላንድ ውስጥ 18 ዓመት ዕድሜ የሞላው ሰው ነው ማግባት የሚፈቀድለት። ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው ስዎችም ማጋባት ይችላሉ። አንድ ወንድ ከአንድ ወንድ ጋር፣ እንደዚሁም አንዲት ሴት ከአንዲት ሴት ጋር መጋባት ይችላሉ። እነሱም እንደ ሌሎች ጥንዶች እኩል መብት አላቸው፣ በዚህም ምክንያት መጋባትም ይፈቀድላቸዋል። መጋባት በሚፈልጉበት ግዜ የነዋሪዎች መመዝገቢያ ጽሕፈት ቤት ማለትም /በሲቪል ማዘጋጃ ቤት/ Basel-Stadt (Zivilstandsamt) ማመልከት አለባቸው። የነዋሪዎች መመዝገቢያ ጽሕፈት ቤቱ የአሰራር ሂደቱን የሚጀምረው (Ehevorbereitungsverfahren)“በጋብቻ ዝግጅት ሂደት“ መሰረት ነው። በዚህ የአሰራር ሂደት ጋብቻው መስመር እንዲይዝ ይደረጋል። ለምሳሌ ያህል ጽ/ቤቱ ሁለቱ ጥንዶች ለመጋባት መስፈርቱን ማሟላታቸውን ያረጋግጣል። የአሰራር ሂደቱ ሲያልቅ ጥንዶቹ በ3 ወራት ውስጥ መጋባት አለባቸው። የነዋሪዎች መመዝገቢያ ጽሕፈት ቤቱ የአሰራር ሂደቱ እንዴት እንደሆነ እና ምን ዓይነት ሰነዶች እንደሚያስፈልጉ መረጃ ይሰጣቸዋል።
ምናልባት አንዳቸው ነዋሪነታቸው ውጪ አገር ከሆነ መጀመሪያ ወደ ስዊዘርላንድ መግባት እንዲፈቀድላቸው ማመልከቻ ማቅረብ አለባቸው (ለመጋባት የሚደረጉ ዝግጅቶች) ። ከዛ በኋላ ሁለቱም እዚህ ስዊዘርላንድ ውስጥ መጋባት ይችላሉ።
የነዋሪዎች መመዝገቢያ ጽሕፈት ቤቱ የይስሙላ ጋብቻ (Scheinehe) ነው ብሎ ጥርጣሬ ሊያድርበት ይችላል። የይስሙላ ጋብቻ (Scheinehe) ማለት: ሁለቱ ጋብቻውን የሚፈጽሙት አንዳቸው ስዊዘርላንድ ውስጥ መኖር እንዲያስችላቸው ብቻ ከሆነ ነው። በዚህም የተነሳ የነዋሪዎች መመዝገቢያ ጽሕፈት ቤቱ ጋብቻውን ውድቅ ሊያደርገው ይችላል። ጋብቻውን ፈጽመው ከሆነም ጽ/ቤቱ ጋብቻውን ውድቅ ሊያደርገው ይችላል። ይህም ማለት ጋብቻው ይፈርሳል ማለት ነው። ምናልባትም በዚህ በይስሙላ ጋብቻ ምክንያት የመቆያ/የመኖሪያ ፍቃዳቸውን ሊያጡ ይችላሉ።