የቤተሰብ ዳግም መቀላቀል ፕሮግራም

ስዊዘርላንድ ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ፣ የቤተሰብዎ አባላቶች ወደ ስዊዘርላንድ ሊመጡ ይችላሉ። ይህ እንዲሆን መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች አሉ። ስዊዘርላንድ ዘመዶችዎ ወይም ጓደኞችዎ እንዲጎበኝዎት ይፈልጋሉ? ከፈለጉ አንዳንድ ጊዜ ለመግቢያ ቪዛ ማመልከት አለባቸው።. ይህም ከየትኛው አገር ጎብኚዎት የሚመጡ መሆኑ ነው የሚወስነው።

የቤተሰብ ዳግም መቀላቀል ፕሮግራም

እዚህ የሚኖሩ ከሆነ፣ ምናልባት የቅርብ ዘመዶችዎን ወይም የትዳር ጓደኛዎን ወደ ስዊዘርላንድ (በቤተሰብዎ ዳግም መቀላቀል ፕሮግራም፣ Familiennachzug) ማምጣት ይችሉ ይሆናል። ለየትኛው የቤተስብዎ አባል ማመልከቻ ማቅረብ ይፈቀድሎታል? ወሳኙ ዜግነትዎ ወይም ምን ዓይነት የመኖሪያ ፈቃድ እንዳለዎት ነው። በግዝያዊነት የመቆያ ፍቃድ ብቻ የተመዘገቡ ከሆነና ማለትም F መታወቂያ የተሰጠዎት ከሆነ፣ ምናልባትም ቤተሰብዎ ተከትለዎት መምጣት ይፈቀድላቸው ይሆናል።

ቤተሰብዎ ከእርስዎ ጋር መቀላቀል ይችሉ እንደሆነ የሚወስነው የስደተኞች አስተዳደር ጽ/ቤት (Migrationsamt) ነው። የስደተኞች አስተዳደር ጽ/ቤት በቀጣይነት ምን ማድረግ እንዳለብዎት እና እንዲሁም ምን ዓይነት ሰነድ እንደሚያስፈልጎት ተገቢውን መረጃ ይሰጥዎታል።

ማሳሰቢያ፣
ቤተሰብዎ ዳግም ከእርስዎ ጋር መቀላቀል እንዲችሉ በተሰጠው የግዜ ገደብ ውስጥ ማመልከት አለብዎት። ለልጆች ከሆነ ገደቡ ከአዋቂዎች ያንሳል፣ ለምሳሌ የትዳር ጓደኛዎን ለማምጣት።

ለጋብቻ ዝግጅት

ስዊዘርላንድ ነው የሚኖሩት እናም ከውጪ አገር ሰው ማግባት ይፈልጋሉ? የመግቢያ ፈቃድ ስለሚያስፈልግ አስቀድሞ ማመልከት ያስፈልጋል፣ ከጋብቻ ዝግጅት ሂደት አካል አንዱ ነው። (Vorbereitung der Heirat). በዚህም አጋርዎ ከመጋባታችሁ በፊት ካሉበት አገር ወደ ስዊዘርላንድ መግባት ያስችላቸዋል፣ በመቀጠልም እዚህ መጋባት ትችላላችሁ።

አጋርዎ የመግቢያ ፈቃድ እንዲሰጠው የሚወስነው የስደተኞች አስተዳደር ጽ/ቤት (Migrationsamt) ነው። የስደተኞች አስተዳደር ጽ/ቤት በቀጣይነት ምን ማድረግ እንዳለብዎት እና እንዲሁም ምን ዓይነት ሰነድ እንደሚያስፈልጎት ተገቢውን መረጃ ይሰጥዎታል።

የመግቢያ ቪዛ

ዘመድዎ ወይም ጓደኞችዎ ከትውልድ አገርዎ እርስዎን ሊጎበኝዎት /ሊጠይቆት/ ወደ ስዊዘርላንድ መምጣት ይፈልጋሉ?

የሚፈልጉ ከሆነ ወደ ስዊዘርላንድ የመግቢያ ቪዛ ያስፈልጋቸዋል። አብዛኛውን ግዜ የመግቢያ ቪዛ ለማግኘት ቀላል አይደለም። አንዳንድ ግዜ እርስዎ የጋበዟቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የግብዣ ወረቀት ማሳየት አለባቸው። ወይም ጎብኚዎቹ ራሳቸውን ፋይናንስ ለማድረግ ዓቅም ያላቸው መሆኑን ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው። (ግዴታ የሚያስገባ ውል፣ Verpflichtungserklärung).

ውጭ አገር የሚገኘው የስዊዘርላንድ ኢምባሲ ቪዛ መሰጠት እንዳለበት ይወስናል። ኢምባሲው ጎብኚዎች በቀጣይነት ምን ማድረግ እንዳለባቸው እና እንዲሁም ምን ዓይነት ሰነድ እንደሚያስፈልጋቸው ተገቢውን መረጃ ይሰጣል። እንዲሁም ከስደተኞች አስተዳደር ጽ/ቤት (Migrationsamt) ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።