አጠቃላይ የአደጋ ግዜ ስልክ ቁጥር፣ 112
በዚህ ቁጥር ወደ ፖሊስ የአደጋ ጊዜ ጥሪ ማእከል መደወል ይችላሉ። እንደ ድንገተኛ ሁኔታው ዓይነት ፖሊስ ለሌሎች አካላት (ለምሳሌ ለእሳት አደጋ መከላከያ) ያሳውቃል።
የአደጋ ጊዜ ቁጥሮች በየዕለቱ በቀን 24 ሰአት ተደራሽ ናቸው። አጠር ያሉ ስልክ ቁጥሮች (3 አሃዞች) ሁልጊዜ ከክፍያ ነጻ ናቸው። ሌሎች ቁጥሮችን ሲደውሉ አብዛኛውን ጊዜ በመደበኛው የስልክ ታሪፍ መሰረት ያስከፍላል።
በዚህ ቁጥር ወደ ፖሊስ የአደጋ ጊዜ ጥሪ ማእከል መደወል ይችላሉ። እንደ ድንገተኛ ሁኔታው ዓይነት ፖሊስ ለሌሎች አካላት (ለምሳሌ ለእሳት አደጋ መከላከያ) ያሳውቃል።
በዚህ ስልክ ቁጥር ወደ ፖሊስ የአደጋ ጊዜ ጥሪ ማእከል መደወል ይችላሉ።
በዚህ ስልክ ቁጥር የእሳት አደጋ መከላከያ ተጠባባቂ ዝግጁ ቡድን ማእከል መደወል ይችላሉ።
በዚህ ስልክ ቁጥር የእሳት አደጋ መከላከያ ተጠባባቂ ዝግጁ ቡድን ማእከል መደወል ይችላሉ። አስቸኳይ እርዳታ እና አምቡላንስ ከፈለጉ ወይም የሁኔታውን አስጊነት መገምገም ካልቻሉ (ለምሳሌ ከአደጋ በኋላ) 144 ቁጥር መደወል አለበት።
በሌሎች የሕክምና ችግሮች በሚመለከት በመጀመሪያ የቤተሰብ ዶክተርዎን ማነጋገር አለብዎት፣. ከአጠቃላይ ሀኪሞች ክሊኒክ የስራ ሰዓት ውጭ፣ ለህይወት አስጊ ባልሆኑ ሁኔታዎች በማንኛውም ጊዜ የህክምና ድንገተኛ ጥሪ ማእከልን (Medizinische Notrufzentrale MNZ) 061 261 15 15 መደወል ይችላሉ። እዚያም የሕክምና እርዳታ ይደረግልዎታል። እና ወደ የሚመለከተው፣ በአቅራቢያ ወዳለ (ሃኪም፣ ሆስፒታል) ይላካሉ። እንዲሁም ወደ የድንገተኛ አደጋ ጣቢያ (ሆስፒታል / የድንገተኛ ጊዜ ክሊኒክ) እራስዎ መሄድ ይችላሉ።.
በዚህ ቁጥር በባዝል-ከተማ የድንገተኛ አደጋ ተረኛ መድሃኒት ቤት (Notfallapotheke) ማግኘት ይቻላል። በፒተርስግራበን 3 የሚገኘው የድንገተኛ አደጋ ተረኛ መድሃኒት ቤት ሁልጊዜም ሌሊት እና በሳምንቱ መጨረሻ ጭምር ክፍት ነው፣ ስለዚህ በድንገተኛ አደጋ ጊዜ መድሃኒት ማግኘት ይችላሉ።
የጥርስ አደጋ በሚከሰትበት ጊዜ ወዲያውኑ የጥርስ ሀኪምዎጋ ይደውሉ። ከመክፈቻ ሰአታት ውጭ ከሆነ፣ የህክምና ድንገተኛ ጥሪ ማእከልን (MNZ) በስልክ ቁጥር 061 261 15 15 ይደውሉ። ይህ ቁጥር በBasel-Stadt ካንቶን የትኛው የጥርስ ሀኪም የድንገተኛ አገልግሎት ተረኛ እንደሆነ ያስታውቆታል።
ምናልባት መርዛማ የሆነ ነገር ከዋጥክ ወይም መርዛማ የሆነ ነገር የዋጥክ ሆኖ ከተሰማህና ከተጠራጠርክ ሃኪሞችና እና ስፔሻሊስቶች በዚህ ቁጥር ብትደውል ሊረዱህ ይችላሉ። መርዝን በሚመለከት ምን እርምጃ መውሰድ እንዳለብህ ይገልጹልሃል።. ለሕይወት አስጊ በሆኑ ሁኔታ ውስጥ ካለህ ግን ወዲያውኑ በፍጥነት 144 ቁጥር መደወል አለብህ። የሚቀጥለው ኢንተርኔት ድረ ገጹ ስለ መርዝና ስለ መመረዝ ጉዳይ ሰፊ መረጃ ይዟል።
በ"ቴሌፎን ቁጥር 143" (ዕርዳታ ለመስጠት የተዘረጉ እጅ፣ Dargebotene Hand) ከሰው ጋር ስለ ለማንኛውም ችግርዎ፣ የፈለገው አይነት ችግር ቢሆን፣ መነጋገር በሚፈልጉበት ግዜ (በጀርመንኛ፣ በፈረንሳይኛ፣ በጣሊያንኛ እና በእንግሊዝኛ) ማውራት ለሚፈልጉ ሰዎች የተዘጋጀ ቁጥር ነው። በአስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ በሚገኙበት ግዜ በችግር ጊዜ፣ ሌላም ችግር ቢያጋጥሞና በጭንቀት ግዜ መደወል ይችላሉ። ውይይቱ በሚስጥር የሚጠበቅ ሲሆን፣ የግድ ማንነቶን መግለጽ አይጠበቅብዎትም። በሚያስፈልጎት ግዜ ለችግርዎ ተስማሚ የሆነ የእርዳታ አቅርቦቶችና መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ። በኢሜል ወይም በቻት ጭምር ግንኙነት ማድረግ ይቻላል።
"ቴሌፎን ቁጥር 147" ከሰው ጋር ስለ ለማንኛውም ችግር፣ የፈለገውም አይነት ችግር ቢሆን፣ መነጋገርና ማውራት ለሚፈልጉ (በጀርመንኛ፣ በፈረንሳይኛ፣ በጣሊያንኛ እና በእንግሊዝኛ) ለልጆች እና ለወጣቶች የተዘጋጀ ቁጥር ነው። የስልክ መስመሩ ስፔሻሊስቶችን ለማግኘት ሁልግዜ ክፍት ነው። በአስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ በሚገኙበት ግዜ በችግር ጊዜ፣ ሌላም ችግር ቢያጋጥምና በጭንቀት ግዜ መደወል ይችላል። ውይይቱ አስተማማኝና በሚስጥር የሚጠበቅ ሲሆን፣ የግድ ማንነትን መግለጽ አይጠበቅም። የስልክ ጥሪው ነጻ ነው፣ ስለዚህም ጥሪው በስልክ ሂሳብ ላይ ክፈሉ የሚል ደብዳቤ አይመጣብዎትም። በኢሜል፣ በኤስ ኤም ኤስ አጭር መልዕክት ወይም በቻት ሊያገኙን ይችላሉ።
በወላጆች የድንገተኛ አደጋ ጥሪ ግዜ (Elternnotruf) ባለሙያዎች ወይም ሌሎች ሰዎች ስለ ልጅ አስተዳደግ ጉዳዮች ጥያቄዎች ካሉ ወላጆችን ይመክራሉ። ከልጆችዎ ጋር ባሎት ግንኙነት ከመጠን በላይ የተጨናነቁ ከሆነ ወይም ጫና ከተሰማዎት ወይም ስለራስዎ ወይም ስለሌላ ሰው ልጅ የሚጨነቁ ከሆነ እርዳታ ያገኛሉ። የእርስዎ ልጅ ወይም ሌላ ልጅ የስነ-ልቦና/አካላዊ ጥቃት ሰለባ ነው ብለው ከሰጉ፣ በወላጆች የድንገተኛ አደጋ ጥሪ ደውለው ማነጋገር ይችላሉ። ውይይቱ አስተማማኝና በሚስጥር የሚጠበቅ ሲሆን፣ ካልፈለጉ የግድ ማንነትዎን መግለጽ አይጠበቅብዎትም። በኢሜልም ጭምር ሊያገኙን ይችላሉ።. የህክምና ጥያቄዎችን በሚመለከት ግን የወላጆች አስቸኳይ የስልክ ጥሪ መስመር ሊረዳዎት አይችልም።
በሁለቱም ባዝሎች የሴቶች መጠለያ (Frauenhaus) ውስጥ በቤት ውስጥ ጥቃት ለተጎዱ ሴቶች የ24 ሰዓት የምክር አገልግሎት እና ድጋፍ ይሰጣል። ዘመዶች እና ባለሙያዎችም ጭምር የመጠለያ ቢሮውን ማነጋገር ይችላሉ። ውይይቱ አስተማማኝና በሚስጥር የሚጠበቅ ሲሆን፣ ካልፈለጉ የግድ ማንነትዎን መግለጽ አይጠበቅብዎትም። የቤት ውስጥ ጥቃት ጉዳይን በሚመለከት፣ ጉዳት ለደረሰባቸው ወንዶችም ጭምር፣ እና የሌሎች ተጨማሪ የመገናኛ ማእከላት እና የምክር አገልግሎት ማእከላት ዝርዝር መረጃ በሄሎ-ባዝልstadt.ch የቤት ውስጥ ጥቃት ምዕራፍ ላይ ይገኛል።