መኪና / ሞተር ሳይክል

በስዊዘርላንድ በደንብ የተገነባ የመንገድ አውታር አለ። የአብዛኞቹ መንገዶች አጠቃቀም ከክፍያ ነፃ ነው። የትራፊክ ደንቦች በጣም አስፈላጊ ናቸው፤ እነዚህ ካልተተገበሩ ቅጣቱ ከፍተኛ ነው፡፡

የትራፊክ ደንቦች

የትራፊክ ደንቦች በስዊዘርላንድ ውስጥ ላሉ መኪና አሽከርካሪዎች በጣም አስፈላጊ ናቸው። ቅጣቱ ከሌሎች አገሮች ጋር ሲወዳደር በጣም ከፍተኛ ነው። በጣም ከባድ በሆኑ የደንቦች መጣስ የመንጃ ፈቃዱን ወደ መነጠቅ ሊያመራ ይችላል፡፡

አንዳንድ አስፈላጊ ህጎች:

  • በከተማ ውስጥ ከፍተኛው ፍጥነት: 50 ኪሜ / በሰዓት- ከከተማ ውጭ፡ 80 ኪሜ በሰዓት፣ ሀይዌይ፡ 100 ኪሜ በሰአት፣ አውራ ጎዳና፡ 120 ኪሜ በሰአት
  • በአውራ ጎዳና፡ ላይ በቀኝ በኩል ማለፍ የተከለከለ ነው። በግራ በኩል ወይም በመካከለኛው መስመር ላይ በመስመር ኮሎን ከተፈጠረ፣ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ በቀኝ በኩል ማለፍ ይፈቀዳል።
  • ብርሃን በቀትር መብራት አለበት፤
  • በመኪና ውስጥ ያለ ሰው ሁሉ መታጠቅ አለበት።
  • ልጆች በህጻን መቀመጫ ውስጥ መሆን አለባቸው (እስከ 12 ዓመት ወይም 150 ሴንቲሜትር ቁመት ድረስ)
  • በሚያሽከረክሩበት ጊዜ ስልክ መደወል የሚፈቀደው ከእጅ ነጻ በሆነ ስርዓት ብቻ ነው።
  • በአልኮል ወይም በአደንዛዥ እጽ ተጽዕኖ ስር ሆኖ ማሽከርከር የሚያስቀጣ ወንጀል ነው (የአልኮል ገደብ 0.5)
  • በእግረኛ ማቋረጫ ላይ ያሉ እግረኞች ሁልጊዜ ቅድሚያ አላቸው (ማቋረጡ በትራፊክ መብራቶች ካልተመራ በስተቀር)

የመንገድ ግብር

መንገዶቹ በኮንፌዴሬሽን፣ በካንቶኖች እና በማዘጋጃ ቤቶች የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግላቸው ናቸው። የመንገዶቹ አጠቃቀም ከክፍያ ነጻ ነው። ልዩ ሁኔታዎች ፈጣን አውራ ጎዳናዎች ናቸው።፡ ፈጣን አውራ ጎዳናዎች መጠቀም የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ቪግኔት (Vignette) በየዓመቱ መግዛት አለበት። ይህ በንፋስ መከላከያው መስተዋት ላይ መለጠፍ አለበት። ቪንቴቶቹ በነዳጅ ማደያዎች፣ በፖስታ ቤት ወይም በመንገድ ትራፊክ ቢሮዎች ይገኛሉ።

ኢንሹራንስ

በስዊዘርላንድ ውስጥ የመድን ዋስትና ያላቸው የሞተር ተሽከርካሪዎች ብቻ ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉት። የሞተር ተሽከርካሪ የ3ኛ ወገን መድን ዋስትና (Motorfahrzeug-Haftpflichtversicherung) በተለያዩ የግል ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ይሰጣል። ኢንሹራንሱ በንብረት እና በተሽከርካሪ ላይ በተሽከርካሪ ጉዳት ለደረሰባቸው ይከፍላል።. በራስዎ መኪና ላይ ለሚደርስ ጉዳት የተለያዩ በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ አጠቃላይ የኢንሹራንስ ፖሊሲዎችም (Kaskoversicherungen) አሉ። ማሳሰቢያ፡- አንድ ሰው በከባድ ቸልተኝነት አደጋ ካደረሰ፣ ኢንሹራንሱ ላይከፍል ይችላል (ለምሳሌ በአልኮል መጠጥ ወይም በአደንዛዥ እፅ ተጽዕኖ ስር ማሽከርከር)፣ የሞተር ተሽከርካሪ 3 ወገን መድን ዋስትና ፣ ከግል ከ3ኛ ወገን መድን ዋስትና ውስጥ አይካተትም።

የሞተር ተሽከርካሪ ከውጭ አገር ማስመጣት

ሞተር ተሽከርካሪዎችን በቋሚነት ወደ ስዊዘርላንድ ማስገባት ከፈለጉ በጉምሩክ ቢሮ መመዝገብ እና ማስቀረጥ አለብዎት። የሚያስገቡት ተሽከርካሪ ቴክኒካዊ ፍተሻ ማድረግ አለበት። የሞተር ተሽከርካሪ የ3ኛ ወገን መድን ዋስትና፣ የስዊስ ተሽከርካሪ ምዝገባ ሰነድ እና የስዊዝ ታርጋ ቁጥር ያስፈልግዎታል። ከBasel-Stadt (Motorfahrzeugkontrolle) የሞተር ተሽከርካሪ መቆጣጠሪያ የበለጠ ዝርዝር መረጃ ማግኘት ይቻላል።

መኪና መጋራት

የመኪና መጋራት ማለት ብዙ ሰዎች በአንድ ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ መኪኖችን አብረው ይጠቀማሉ ማለት ነው። የመኪና ማጋሪያ ድርጅት ተሽከርካሪዎች ብዙውን ጊዜ በተከራዩ የመኪና ማቆሚያ ቦታዎች ውስጥ ናቸው፣ እና በቅድሚያ በመስመር በኦን ላይን ወይም በመተግበሪያ በኩል ይታዘዛሉ። ቦታዎቹ ብዙውን ጊዜ በሕዝብ ማመላለሻ ማዕከሎች (ለምሳሌ ባቡር ጣቢያዎች፣ ትራም መገናኛዎች፣ የአውቶቡስ መስመሮች የመጨረሻ ጣቢያዎች) ናቸው። መጋራቱ ከመኪና ኪራይ የሚለየው ተሽከርካሪውን ለአጭር ጊዜ መጠቀም መቻሉ ነው፣ ለምሳሌ በሰዓት፣