ስለ ባዝል ከተማ

ካንቶን Basel-Stadt የባዝል ከተማ ካንቶን ከ26ቱ የስዊዘርላንድ ካንቶኖች ክልሎች አንዷ ናት። Basel-Stadt በጀርመንና በፈረንሳይ 3 ማዕዘን ድንበር ላይ ትገኛለች። ክልሉ ጠንካራ የሆነ ኢኮኖሚና የተለያየ አይነት ባህል የሚንጸባረቅበትና የላቀ የኑሮ ደረጃ የሚታይበት ነው።

አሃዞች እና እውነታዎች

Basel-Stadt ሶስት ቀበሌዎችን/አውራጃዎችን/ ያቀፈ ነው። ከባዝል ማዘጋጃ ቤት እና ከሁለቱ ከሪሀን እና ቤቲንገን ፖለቲካዊ የኮምዩን አስተዳደሮችን (Gemeinden) ያጠቃልላል። ካንቶኑ ውስጥ ከ 200,000 በላይ የሚሆኑ ከ160 አገሮች የመጡ ሰዎች ይኖሩባታል። Basel-Stadt 37 ካሬ ሜትር ብቻ የቆዳ ስፋት ኣላት። ስዊዘርላንድ ውስጥ ትንሿ ካንቶን ስትሆን በትንሽ ቦታ ጥቅጥቅ ያለና ብዙ ሰዎች የሰፈሩበት ቦታ ነው። የክልሉ /የካንቶኑ/ የመነጋገሪያ ቋንቋ ጀርመንኛ ነው።

ታሪክ

Basel-Stadt የተመሰረተችው በ1833 ነው ። ከተማዋ ትልቅና የሚያጓጓ ታሪክ አላት። ጥንት ከ130.000 ዓመታት በፊት ከመካከለኛው የድንጋይ ዘመን ግዜ ጀምሮ ሰዎች ሰፍረውባት ነበር። Basel ስታርቴጅያዊ በሆነ ቦታ ስለምትገኝ፣ ሮማውያን ከክርስቶስ ልደት ከ30 ዓመት በፊት የሙንስተር ኮረብታ ላይ ወታደሮቿን አስፍረው ነበር። እዛው ቦታ ላይ በአሁኑ ሰዓት የባዝል ሙንስተር ካቴድራል ይገኛል። ይህ ካቴድራል ከዚህ ቀደም የጳጳሱ ቤተ ክርስትያን ነበር፣ ቤተ ክርስትያኑም የተመረቀው በ 1019 ነው። በዚህም የተነሳ የባዝል ሙንስተሩ ካቴድራል ላይ የካንቶኑ ዓርማ የሆነው የባዝል የከዘራ ምስል የሚታየው፣ ይህም የጳጳሱን ከዘራ ነው የሚያመለክተው።
የባዝል ዩንቨርስቲ የተመሰረተው በ1460 ነው። ባዝል ወደ መጽሐፍ ህትመት እንዲሁም ወደ Humanismus /የሰብዓዊነት ጥናት/ ማዕከልነት እየጎለበተች መጣች። በ 16 ኛው ክፍለ ዘመን ከላይኛው ጣልያን ግዛትና ከፈረንሳይ ብዙ ስደተኞች ወደዛ ይፈልሱ ነበር። እነሱም የሃር ስራንና የሃር ማቅለምን ጥበብ ወደ ባዝል ይዘው መጡ። የዛሬዎቹ የመድሃኒትና የኬሚካል እንዱስትሪዎች የዚህ ውጤት ናቸው። በ1833 የBasel-Stadt እና የBasel-Landschaft ከጦርነት ግጭት በኋላ ተለያዩ። ዛሬ Basel-Stadt የባህል፣ የንግድ እና የኢኮኖሚ ማዕከል ስትሆን በዋናነትም የህይወት ሳይንስ ማዕከል ናት።

ልምድ እና ባህል

በካንቶን Basel-Stadt ብዙ ተለምዶዎችና ባህሎች አሉን፣ እነሱም ለኛ በጣም አስፈላጊዎቻችን ናቸው። ተለምዶዎቻችንና ባህሎቻችንን ለማወቅ ፍላጎት ካላችሁ በጣም ደስ ይለናል። ከሁሉም በመጀመሪያ ደርጃ የሚከበረው ፋስናኽት (Fasnacht) በዓል ነው።. ይህ በዓል በየዓመቱ የካቲት ወይም ሚያዝያ ለሶስት ቀናቶች ይካሄዳል። ለዚያም ነው እኛ «drey scheenschte Dääg» ሶስቱ ምርጥ ቀኖች ብለን የምንጠራው። የባዝል የበልግ ትርኢት (Herbstmesse) ከ 500 ዓመት በላይ ዕድሜ ያለው ነው። እንደዚሁም የባዝል የገና ገበያ (Weihnachtsmarkt) ረጅም ጊዜ የቆየ ባህል ነው። ብዙ ሰዎች ማህበራት፣ የክለባትና የማህበራዊ ተቋማት ኣባላት ናቸው። የባዝል እግር ኳስ ክለብ ጨዋታ ላይ ብዙ ተመልካቾች ይገኛሉ፣ እንዲሁም በበጋ ወቅት ብዙ ሰዎች ራይን ወንዝ ላይ ይዋኛሉ።