ሃይማኖትና መንግስት (DE)
ስዊዘርላንድ በተለምዶ በክርስቲያን ሃይማኖት የተቀረጸች ሃገር ናት። ካንቶኖቹ በሃይማኖትና በመንግስት መካከል ያለውን ዝምድና ይወስናሉ። እንደ አብዛኞቹ ጀርመንኛ ተናጋሪ የስዊስ ካንቶኖች ሁሉ የBasel-Stadt ካንቶን ለአንዳንድ የሃይማኖት ማህበራት ልክ እንደ የህዝብ ተቋማት እውቅና ይሰጣሉ። ይህም ማለት መንግስት ለእነሱ የተወሰኑ መብቶችን ያስተላልፋል ማለት ነው። ለምሳሌ አባሎቻቸውን ታክስ ማስከፈል ይችላሉ። የሚከተሉት የሃይማኖት ማህበራት በBasel-Stadt ካንቶን በግልጽ የሕግ ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል: የኢቫንጀሊካል ተሐድሶ ቤተ ክርስቲያን፣ የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን፣ የክርስቶስ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እና የአይሁድ ማኅበረሰብ፣ ሌሎች አንዳንድ ተጨማሪ ማህበራትም በካንቶን ተቀባይነትን ያገኙ አሉ። እነዚህ ማህበራት በግል በሕግ የተደራጁ ናቸው።