ባህል

ባዝል ከተማ ውስጥ ብዙ የባህላዊ ዝግጅቶች ይካሄዳሉ። ብዙ ገንዘብ ከሌለዎት፣ ያለ ክፍያ ወም በነጻ የመጠቀም ብዙ አማራጮች አለዎት።

ሙዚየሞች / ኢግዚቢሽኖች

ወደ አርባ የሚጠጉ ሙዚየሞችና ኤግዚቢሽኖች ዝግጅቶችን ያቀርባሉ። በተጨማሪም ብዙ ትናንሽ ጋለሪዎች እና አማራጭ የጥበብ ስራ ውጤቶችን ማሳያ ቦታዎችን መጎብኘት ይችላሉ። ለሕዝብ ክፍት በሆኑ ቦታዎች ብዙ የጥበብ ሥራዎችን መጎብኘት ይቻላል።

ሙዚቃ / ዳንስ / ቲያትር / ስነ ጽሑፍ (DE)

በBasel-Stadt ካንቶን ውስጥ ብዙ ባህላዊ ዝግጅቶች ይካሄዳሉ። በTheater Basel ውስጥ ኦፔራ፣ ድራማ እና ባሌት እንዲሁም በKaserne ዘመናዊ ሙዚቃ፣ ዳንስ ወይም ቲያትር በማየት መደሰትይችላሉ። እንደ Vorstadttheater ወይም የSommercasino ያሉ ትናንሽ ቦታዎችም አሉ። በበጋ ወቅት ብዙ የውጪ ትርኢቶች እና ፌስቲቫሎችን መጎብኘት ይችላሉ። አንዳንድ ዝግጅቶችም ከክፍያ ነጻ ናቸው።

አርክቴክቸር

በባዝልና በአካባቢው ብዙ ዘመናዊ የአርክቴክቸር ስራዎችን ማድነቅ ይቻላል። ለምሳሌ በአርክቴክት ሬንዞ ፒያኖ የተሰራው Fondation Beyeler በራይን ማየት ይቻላል። በባዝል መሃል ከተማ በChrist & Gantenbein አርክቴክቸር ቢሮ የKunstmuseums Basel አዲስ ህንፃ ግንባታ ወይም በHerzog & de Meuron አርክቴክቸር ቢሮ የStadtcasinos Basel ቀጣይ ማስፋፊያ ግንባታ ይታያል።

ባህልን ማበረታቻዎች

በሙያዎ አርቲስት ከሆኑ ለፕሮጀክትዎ የገንዘብ ድጋፍ ማመልከት ይችላሉ። ለምሳሌ ያህል የገንዘብ ድጋፍ እንዴት ማመልከት እንደሚቻል በባህል ቢሮ ድረ ገጽ ላይ የበለጠ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

ከክፍያ ነጻ እና ቅናሽ አቅርቦቶች

ብዙ ሙዚየሞችና ባህላዊ ዝግጅቶች የሚደረግባቸው ቦታዎች ልዩ የሆነ የዋጋ ቅናሽ አቅርቦቶች አላቸው። ለምሳሌ ያህል በተወሰኑ ወቅቶች ነጻ መግቢያ ወይም ያነሰ ክፍያ ይጠይቃሉ። ለተወሰኑ ሰዎች መግቢያ አብዛኛውን ግዜ ቅናሽ ወይም ነጻ ነው። በተጨማሪም ክፍያ የሌላቸው ነጻ ዝግጅቶች ወይም ፌስቲቫሎች ለህዝብ ክፍት በሆኑ ቦታዎች ይዘጋጃሉ። ብዙ ማህበራት (Vereine) እና ድርጅቶች ስደተኝነትን በተመለከተ ባህላዊ ዝግጅቶችና አቅርቦቶች አላቸው። በKulturLegi የቤተሰብ ካርድ (Familienpass) ወይም በcolorkey ላላቸው ሰዎች ብዙ ቅናሽ አቅርቦቶች አሉ። ብቻዎትን ወደ ሙዚየም መሄድ አይፈልጉም? በግሩፕ ወይም በTandem ጥንድ ለሆኑ ሰዎች የተለያዩ ቅናሽ አቅርቦቶች አሉ። "Tandem" ማለት: ከሌላ አንድ ሰው ጋር በጥንድ ዝግጅቱን የሚካፈሉ ከሆነ ነው።