ልጆች

በቤት ውስጥ ጥቃት የሚደርስባቸው ልጆች እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።

የቤት ውስጥ ጥቃት በልጆች ላይ ሌላ ጠንቅ ያመጣባቸዋል።

ልጆች በቤት ውስጥ የቤት ውስጥ ጥቃት ሲደርስባቸው በእድገታቸው ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ያሳድርባቸዋል። ይህ የሚሆነው ልጆች ቀጥተኛ የጥቃት ዓላማ እንኳን ባይሆኑም ነው።

አንዳንድ ልጆች ዝም በማለት ይሰቃያሉ፣ ሌሎች ደግሞ የተለያዩ ምልክቶችን ያሳያሉ። ለምሳሌ፡- በትምህርት ቤት ውስጥ ያሉ ችግሮች፣ አልጋን ማርጠብ፣ ራስ ምታት፣ የአመጋገብ ወይም የእንቅልፍ መዛባት፣ ከሌሎች ልጆች ጋር የመገናኘት እና የመግባባት ችግሮች ወይም የጠበኝነት ምልክቶችን ያሳያሉ።

እነዚህ ኤጀንሲዎች ለልጆች ድጋፍ ይሰጣሉ

የጥቃት ሰለባ ለሆኑ ድጋፍ ስጪ የምክር አገልግሎት ማእከላት (Opferhilfe) ልጆች የቤት ውስጥ ጥቃት ሲደርስባቸው የምክር አገልግሎት ይሰጣሉ። ስለ ድጋፍ ስጪ የምክር አገልግሎት ማእከላት ተጨማሪ መረጃ እዚህ ያገኛሉ።

የልጆች እና የወጣቶች አገልግሎት የአስተዳደግ ቢሮዎች KJD (Kinder- und Jugenddienst KJD) የልጆች እና የወጣቶችን ጤናማ እድገት በሚመልከት ልጆች እና ወጣቶች እዚያ እርዳታ ያገኛሉ፣ ለምሳሌ በቤተሰብ ግጭቶች የተነሳ።

ልጆች ምን ማድረግ ይችላሉ? (DE)

በቤት ውስጥ ጥቃት የሚደርስባቸው ልጆች ከቤተሰብ ውጭ ካለ ሰው ጋር ስለ ጉዳዩ ቢነጋገሩ መልካም ነው። ለምሳሌ፡- ከአስተማሪዎች ፣ ከትምህርት ቤቱ የማህበራዊ ሰራተኞች፣ ከጓደኞቻቸው ወላጆች ወይም ከጎረቤቶች ጋር።

Pro Juventute ቀንና ሌሊት ስልክ መደወል ይቻላል። ስፔሻሊስቶቹ ስለ ውይይቱ ስለ ንግግሩ ለማንም አይናገሩም። እነሱም በደንብ ካዳመጡ በኋላ ለተጎጂዎቹ መፍትሄ እንዲያገኙ እርዳታን ይሰጣሉ። ወደ Pro Juventute የሚደረጉ ጥሪዎች ከክፍያ ነጻ ናቸው። ደዋዮች የግድ ስማቸውን መግለጽ አይጠበቅባቸውም። Pro Juventute በጽሑፍ መልእክት፣በቻት ወይም በኢሜል ማግኘት ይቻላል።