ከሚከተሉት ተቋማት እርዳታ ያገኛሉ

የቤት ውስጥ ጥቃት (Häusliche Gewalt) ማለት በቤተሰብ ውስጥ ወይም በአጋርነት መሃከል የሚያጋጥም ጥቃት ማለት ነው ። በቤት ውስጥ ለሚያጋጥም ጥቃት እርዳታ ማግኘት አስፈላጊ ነው። የተለያዩ ማእከላት መረጃ፣ ምክር አገልግሎት እና ድጋፍ ይሰጣሉ። ይህም ብዙውን ጊዜ ሚስጥራዊ፣ ብዙ ጊዜ ከክፍያ ነጻ እና አስፈላጊ ከሆነም ከአስተርጓሚ ጋር በመተባበር የሚተገበር ነው። እነዚህ ቦታዎች እርዳታ ማግኘት ይቻላል።

በድንገተኛ አደጋ ጊዜ

በድንገተኛ ጊዜ እርዳታን በተመለከተ ተጨማሪ እንደሚከተለው ( ከሚቀጥለው) መረጃ ማግኘት ይቻላል።

  • ፖሊስ፡ 112 / አምቡላንስ፡ 144
  • ጥበቃ፣ ምክር እና ልጅ ላላቸው እና ልጆች ለሌላቸው ሴቶች መጠለያ ፡ Frauenhaus በባዝል (24/7)፣ 061 681 66 33፣ www.frauenhaus-basel.ch
  • ጥበቃ፣ ምክር እና ልጅ ላላቸው እና ልጆች ለሌላቸው ሴቶች መጠለያ ፡ ለሴቶች እና ለልጆች መኖሪያ ቤት (24/7)፣ 061 302 85 15፣ https://wohnen-frauen-kinder.heilsarmee.ch (DE)
  • የህክምና እርዳታ ለሴቶች፡ የሴቶች ክሊኒክ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ድንገተኛ አደጋ (24/7)፣ 061 328 75 00፣ www.unispital-basel.ch/frauenklinik
  • የህክምና እርዳታ ለህፃናት፣ ለህጻናት እና ለወጣቶች የህክምና እርዳታ፡ የባዝል ዩኒቨርሲቲ የህጻናት ሆስፒታል የድንገተኛ አደጋ (24/7)፣ 061 704 12 12፣ www.ukbb.ch
  • የህክምና እርዳታ፡ የባዝል ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የድንገተኛ አደጋ ማእከል (24/7)፣ 061 265 25 25፣ www.unispital-basel.ch/notfallzentrum
  • በችግር ጊዜ ጣልቃ ገብነት፣ በስነ ልቦናዊ ችግሮች እገዛ፡ የባዝል ዩኒቨርሲቲ የሳይካትሪ ክሊኒኮች የድንገተኛ አደጋ ክፍል (24/7)፣ 061 325 51 00፣ www.upk.ch

የምክር አገልግሎት

አስተማማኝ ሚስጥራዊ እና የነፃ ምክር አገልግሎት። ተርጓሚ ሊቀርብ ይችላል።

  • ለሴቶች፣ ለወንዶች፣ ለልጆች እና ለወጣቶች ምክር፣ እርዳታ እና የገንዘብ ድጋፍ፡ በባዝል፣የተጎጂዎች እርዳታ፣ 061 205 09 10፣ www.opferhilfe-beiderbasel.ch
  • የችግር ጣልቃገብነት እና ምክር፡ የካንቶናል ፖሊስ ማህበራዊ አገልግሎት (የቤት ውስጥ ጥቃት የካንቶኖች ፖሊስ መምሪያ)፣ 061 267 70 38
  • ስለ አልኮል እና ሱስ ችግሮች የምክር አገልግሎት፡- የጤና ዲፓርትመንት፣ የሱስ መቆጣጠሪያ መምሪያ ክፍል፣ 061 267 89 00፣ www.bs.ch/gd/sucht (DE)
  • በተለያዩ ቋንቋዎች ስለ ሱስ ችግሮች የምክር አገልግሎት፡- ፡ የመድብለ ባህላዊ የሱስ የምክር አገልግሎት ማእከል MUSUB, 061 273 83 05, www.mituns.ch
  • ማንነትዎን ሳይገልጡ የሚሰጥ የምክር አገልግሎት፡- (በስልክ፣ በቻት እና በኢሜል)፡ እርዳታ ለማግኘት (24/7)፣ ስልክ 143 ይደውሉ፣ www.143.ch ድረ-ገጽ ይጎብኙ፣
  • እርዳታ እና የምክር አገልግሎት፡ ለወላጆች፣ ለቤተሰቦች እና ለተንከባካቢዎች፡ የወላጅ የአደጋ ጊዜ ጥሪ (24/7)፣ 0848 35 45 55 (የመደበኛ የቤት ስልክ ታሪፍ)፣ www.elternnotruf.ch ድረ-ገጽ ይጎብኙ፣
  • ምክር ለሚፈልጉ ወንዶች መማክርት፡ ባዝል ክልል የወንዶች ጽ/ቤት 061 691 02 02, www.mbrb.ch (DE) የምክር አገልግሎት ዋጋ የሚወሰነው ምክር በሚፈልገው ሰው የገንዘብ ዓቅም ላይ ተመርኩዞ ነው።

ልጆች እና ወጣቶች

አስቸጋሪ የቤተሰብ ችግር ያለባቸው ህጻናት እና ወጣቶች ወደ ፕሮ ጁቬንቱንት (Pro Juventute) ቀንም ሆነ ሌሊት በመደወል ማመልከት ይችላሉ። በስልክ፣ በጽሑፍ መልእክት ወይም በኢሜል መነጋገር እና መወያየት ይቻላል።

  • ህጻናት እና ወጣቶች ማንነታቸውን ሳይገልጡ በስልክ፣ በውይይት፣ በጽሑፍ መልእክት ወይም በኢሜል እርዳታ ማግኘት ይችላሉ። Pro Juventute: ሚስጥራዊ እና ነፃ ምክር 24/7 በስልክ ቁጥር 147፣ እንዲሁም www.147.ch ድረ-ገጽ መጠቀም ይችላሉ፣

የሕክምና ዕርዳታ እና ጭብጥ የፎረንሲክ ማረጋገጫዎች

አካላዊ እና ወሲባዊ ጥቃትን በተመለከተ፣ በተቻለ ፍጥነት የዶክተር ምርመራ በቶሎ እንዲያገኙ ይመከራሉ። ምርመራው ሚስጥራዊ ነው። የተጎዳው ሰው ይህን መግለፅ ፍቃደኛ ከሆነ ብቻ ለፖሊስ የሚነገረው ነው።

የባዝል ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል በአካልና በፆታዊ ጥቃት ላይ ጉዳት ለደረሰባቸው እና ማስረጃዎችን በማግኘት ላይ ያተኮረ ምርመራ በማድረግ የተዋጣለት ነው። ሌላ ቦታ ሂዶ ህክምና የሚፈልግ ማንኛውም ሰው፣ የጥቃት ምልክቶችን በዝርዝር እንዲመዘግብ ሐኪሙን መጠየቅ አለበት።

  • ለሴቶች፡ የሴቶች ክሊኒክ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ለድንገተኛ አደጋ (24/7)፣ 061 328 75 00፣ www.unispital-basel.ch/frauenklinik , Spitalstrasse 21 ይጠቀሙ፣
  • ለወንዶች፡ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ባዝል የድንገተኛ አደጋ ማዕከል (24/7)፣ 061 265 25 25፣ www.unispital-basel.ch/notfallzentrum ይጠቀሙ፣
  • በአቅራቢያው በሚገኝ ሆስፒታል የቤተሰብ ዶክተር ልምምድ ወይም ድንገተኛ ሆስፒታል
  • ለተጎጂዎች እርዳታ በባዝል፣ 061 205 09 10፣ www.opferhilfe-beiderbasel.ch ይጠቀሙ፣

ለጥቃት ፈፃሚዎች የምክር አገልግሎት

ሚስጥራዊ እና አስተማማኝ አገልግሎት፣ ከትርጉም ጋር፣

  • ለቤት ውስጥ ጥቃት በሚመለክት ማማከር፡- በቤት ውስጥ ጥቃት ለተፈጸመ ግጭት የምክር አገልግሎት፣ 061 267 44 90 www.bs.ch (DE)
  • ምክር ለሚፈልጉ ወንዶች መማክርት፡ በባዝል ክልል የወንዶች ጽ/ቤት 061 691 02 02፣ www.mbrb.ch (DE) የምክር አገልግሎት ዋጋ የሚወሰነው ምክር በሚፈልገው ሰው የገንዘብ ዓቅም ላይ ነው።

ሌሎች የመገናኛ ማዕከላት

"ጥቃት ይቁም" (Halt Gewalt) የተሰኘው ድረ ገጽ የቤት ውስጥ ጥቃት ሌሎች ሊረዱ የሚችሉ ቦታዎችን ይዘረዝራል።

ለምሳሌ፣ በስደት መስክ ላሉ ጥያቄዎች፣ የሱስ ምክር፣ የሕግ ምክር ወይም በአስቸጋሪ የቤተሰብ ሁኔታዎች፣