አብሮ መኖር በስዊዘርላንድ

እያንዳንዱ አገር ለየት የሚያደርገው የራሱ የሆነ ባህል አለው። ስዊዘርላንድ ውስጥም ከህብረተሰቡ ጋር አንዴት ተግባብቶ መኖር ማወቅ ያለብዎት ነገር አለ። በስዊዘርላንድ ውስጥም ተግባብቶ ለመኖር እንዲቻል ማወቅ ያለብዎት አንዳንድ ስነ ምግባሮች አሉ።

የተለያዩ ዓይነት ባህሎች

ስዊዘርላንድ ውስጥ የተለያዩ ዓይነት ባህሎችና አስተሳሰቦች አሉ። ይህም አገሪቱ ውስጥ ባሉት አራት ብሔራዊ ቋንቋዎች ላይ የተመረኮዘ ነው። ጀርመንኛ ተናጋሪ በሆኑ የስዊዘርላንድ ቦታዎች የተለመደው ነገር፣ ፈረንሳይኛ ተናጋሪ ከሆኑ የስዊዘርላንድ ቦታዎች ፈጽሞ የተለየ ሊሆን ይችላል። በከተሞችና በገጠር መካከልም ትልቅ ልዩነቶቹ ሊኖሩ ይችላሉ። ይሁን እንጂ በመላው ስዊዘርላንድ ተመሳሳይ የሆኑ ባህሎች አሉ።

የሰላምታ አሰጣጦች

ስዊዘርላንድ ውስጥ እንደሚከተለው ሰላም እንባባላለን። አብዛኛውን ግዜ በመጨባበጥ ሰላም እንባባላለን። ሰላም በምንባባልበት ግዜም ዓይን ለዓይን እንተያያለን። በባዝል "Griezi" እንላለን። በጣም የሚተዋወቁ ሰዎች "Sali" ወይም "Hoi"ይባባላሉ። ከከተማ ውጪ ገጠር አካባቢ ሰዎች መንገድ ላይ ሲገናኙ፣ ባይተዋወቁም እንኳን ሰላምታ ይለዋወጣሉ።

ትህትና ስዊዘርላንድ ውስጥ በጣም አስፈላጊ ነው። በዚህም የተነሳ አብዛኛውን ግዜ አመሰግናለሁ "Danke" እና እባክህን Bitte"እንላለን። ለምሳሌ ገበያ ውስጥ ወይም ሪስቶራንት ውስጥ በተደጋጋሚ "Danke" እና "Bitte"እንባባለለን።

ቀጠሮ ማክበር

ስዊዘርላንድ ውስጥ ቀጠሮ ማክበር በጣም አስፈላጊ ነው፣ በተለይ ደግሞ በስራ ቦታ ላይ። ከ5 ደቂቃ በላይ ዘግይተው የሚመጡ ከሆነ፣ አስቀድመው ማሳወቅ አለብዎት። ከሰው ጋር መገናኘት ይፈልጋሉ? ከፈለጉ አስቀድመው ቀጠሮ ይያዙ።

ቀጥታዊ ያልሆነ ግንኙነት

አብዛኛውን ግዜ ስዊዘርላንድ ውስጥ ትችትን በቀጥታ አንገልጽም። ብዙውን ግዜ በመላ ፍንጭ ነው የምንሰጠው። ቢሆንም ትችታችንን ሰዎች በሚረዱት መልክ አድረገን ነው የምንገልጸው። የጀርመንኛ ቋንቋ በቂ የሆነ ዕውቀት ከሌለዎት፣ ለርስዎ በተለይ ሁኔታውን ለመረዳት በጣም ይከብዶታል። ከዚህም ባለፈ አንዳንድ ጊዜ ግጭቶችን እናስወግዳለን። ጎረቤትዎ በርስዎ የተነሳ የመረበሽ ስሜት ይሰማቸዋል? የሚሰማቸው ከሆነ በአካል ወደነሱ መሄድ ሳይሆን፣ ይልቁንም ደብዳቤ ቢጽፉላቸው ይመረጣል። በትክክል የተረዳዎት መሆኑን ለማወቅ እርግጠኛ ካልሆኑና ከተጠራጠሩ፣ ጉዳዩን በትክክል ለመረዳት ደግመው ቢጠይቁ ይመረጣል።