የቤት እንስሳ ማኖር
በኪራይ ቤት ውስጥ የሚኖር ሰው፣ ጥቃቅን እንስሳዎች እንደ ጊኒ አሳማ፣ ሃምስተር /ትንሽ አይጥ/፣ የካናሪያ ወፎች ወይም አሳዎች የመሳሰሉ ማኖር ይፈቀድለታል። ነገር ግን በኪራይ ውል ውስጥ ትላልቅ እንስሳትን ማኖርና ማቆየት (ድመቶችን ወይም ትናንሽ ውሻዎችን ጭምር) ክልክል ሊሆን ይችላል። እንዲሁም ጫጫታ የሚፈጥሩ እንስሳት ወይም አደገኛ የሆኑ እንስሳትን በሚመለከት የቤት አከራዩ መከልከል ይችላል። በተጨማሪም የእንስሳት ባለቤቶች የእንስሳት ጥበቃ ሕጎችን ማክበር አለባቸው። ለምሳሌ አንዳንድ እንስሳቶች ለብቻቸው መሆን የሌለባቸው እንስሳት ብቻቸውን ማኖር አይፈቀድም (ለምሳሌ ያህል ጥንቸል)።. እንዲሁም የኬጅ/የእንስሳት ጎጆ/ መጠን እና መሳሪያዎችን በሚመለክት አነስተኛ መስፈርቶች አሉ።. ብዙ እንስሳት (ብርቅዬ እንስሳት) ወደ ስዊዘርላንድ እንዲገቡ አይፈቀድም። በተረፈ ለሌሎች እንስሳት የእንስሳት ህክምና ተቋም ልዩ ፈቃድ ያስፈልጋል።