ኦፊሻላዊ ምዝገባ
ወደ Kanton Basel-Stadt ካንቶን ለመኖር የመጡ አዲስ የሆኑ ሰዎች በ 14 ቀናት ውስጥ አዲስ በሚኖሩበት መኖሪያ ቦታ በሚገኝ በነዋሪዎች ምዝገባ ቢሮ (Basel, Riehen ወይም Bettingen) መመዝገብ አለባቸው።
ከስዊዘርላንድ ወይም ከአውሮፓ ህብረት ወይም ከአንዱ /EFTA/ከአውሮፓ ነጻ የንግድ ቀጠና ማህበር አገር ከሆኑ፣
በጽሑፍ ወይም በ E-Umzug CH/ምዝገባ በኤለክትሮኒክ መንገድ/ ወይም Basel-Stadt, Riehen oder Bettingen በሚገኙ በነዋሪዎች ምዝገባ ቢሮ በአካል ቀርበው መመዝገብ ይችላሉ። ከአውሮፓ ህብረት ወይም ከአንዱ /EFTA /ከአውሮፓ ነጻ የንግድ ቀጠና ማህበር አገር ካልሆኑ ግን፣ እባክዎን ወደ ነዋሪዎች ምዝገባ ቢሮ (Einwohneramt) ወደ Spiegelhof የደንበኞች ማዕከል ይምጡ። እዛም ባዮሜትሪክ መረጃዎ መመዝገብ አለበት። ለምዝገባ ያስከፍላል።
የመመዝገቢያ አድራሻው እንደሚከተለው ነው።
Kundenzentrum Spiegelhof
Spiegelgasse 6
4001 Basel
Tel. 061 267 70 60
ለመመዝገብ ምን ያስፈልጎታል? ምን ዓይነት ሰነድ ይዘው መቅረብ እንዳለብዎት እባክዎን አስቀድመው ስለሁኔታው በደንብ ይረዱ። የሚያቀርቧቸው ሰነዶች በጀርመንኛ፣ በፈረንሳይኛ፣ በጣልያንኛ ወይም ከሆኑ ተቀባይነት አላቸው።
ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ሰነዶች የግድ አስፈላጊ ናቸው፣
- የመመዝገቢያ ፎርም (Anmeldeformular). የመመዝገቢያ ፎርም አስቀድመው መሙላት አለብዎት።
- ጊዜው ያላለፈበት (ለEU/EFTA) የሚያገለግል የጉዞ ፓስፖርት ወይም የመታወቂያ ወረቀት ከለር ኮፒ
- የቤት ኪራይ ውል ወይም የመኖሪያ ካርድ ኮፒ
ለማንኛውም በተጨማሪ እነዚህ ሰነዶች ያስፈልጎት ይሆናል፣
- ቪዛ
- የስራ ውል
- የወንጀል ሪከርድ መግለጫ
- የጋብቻ ሰርተፊኬት
- እና ሌሎች ተጨማሪ ሰነዶች
በአንድ ካንቶን ውስጥ የቤት አድራሻዎትን ቢቀይሩ ወይም ከባዝል ከተማ ቢቀይሩ፣ የነዋሪዎች ምዝገባ ቢሮ ሄደው መመዝገብና ማስታወቅ አለብዎት።
ከአውሮፓ ህብረት ወይም ከአንዱ /EFTA/ ከአውሮፓ ነጻ የንግድ ቀጠና ማህበር አገር ካልሆኑ፣ ሆኖም ግን ስዊርላንድ ውስጥ ነዋሪ ከሆኑ፣
ከአንድ ካንቶን ወደ ሌላ ካንቶን ከመቀየርዎ በፊት አስቀድመው የካንቶን Basel-Stadt የኢሚግሬሽን ቢሮ የስምምነት ፍቃድ መስጠት አለበት። መመዝገብ የሚቻለው ፍቃድ ካገኙ በኋላ ነው።