አደንዛዥ ዕጽ
በሕግ ያልተፈቀደ አደንዛዥ ዕጽ ይዞ መገኘት፣ መሸጥና መጠቀም በሕግ ያስቀጣል። አነስተኛ መጠን ቢሆንም እንኳን ያስቀጣል። የትኞቹ ንጥረ ነገሮች ሕገ-ወጥ እንደሆኑ በአደንዛዥ ዕጽ ሕግ (Betäubungsmittelgesetz) ላይ ተደንግጓል። በንግድ መልክ አደንዛዥ ዕጽ መሸጥ ከፍተኛ ቅጣት ያስቀጣል።
አደንዛዥ ዕጽ ተይዞ የተገኘ፣ ተጠቃሚ የሆነ ወይም ሲሸጥ የተገኘ ሰው በህግ ይቀጣል። አልኮል እና ትምባሆ ለመገበያየት የዕድሜ ገደብ አለው።
በሕግ ያልተፈቀደ አደንዛዥ ዕጽ ይዞ መገኘት፣ መሸጥና መጠቀም በሕግ ያስቀጣል። አነስተኛ መጠን ቢሆንም እንኳን ያስቀጣል። የትኞቹ ንጥረ ነገሮች ሕገ-ወጥ እንደሆኑ በአደንዛዥ ዕጽ ሕግ (Betäubungsmittelgesetz) ላይ ተደንግጓል። በንግድ መልክ አደንዛዥ ዕጽ መሸጥ ከፍተኛ ቅጣት ያስቀጣል።
አልኮል እና ትምባሆ ለመገበያየት የዕድሜ ገደብ አለው። የትንባሆ ውጤቶችን እና አልኮላዊ መጠጦችን Basel-Stadt ካንቶን ውስጥ ለልጆች እና ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ለሆናቸው ወጣቶች መሸጥ ክልክል ነው። አንዳንድ እንደ ስፕሪቶዘ /Spirituosen/ ያሉ አልኮላዊ መጠጦች ለነዚህ ዓይነት መጠጦች የዕድሜ ገደቡ 18 ዓመት ነው።
ስዊዘርላንድ ውስጥ ያሉ ካንቶኖች የማጨስ እገዳን በሚመለክት የተለያየ ሕግ አላቸው። የካንቶን Basel-Stadt የማያጨሱ ሰዎችን ደህንንነት ለመከላከል ሲባል፣ እገዳው በፌደራላዊ ሕግና በካንቶኑ የመስተንግዶ ሕግ / Gastgewerbegesetz/ ላይ የተመሰረተ ነው።
ማጨስ የተከለከለባቸው ቦታዎች፣
ሪስቶራንት ውስጥ ማጨስ መቻሉ ወይም አለመቻሉ፣ የሪስቶራንቱ ትልቅነት ነው የሚወስነው። አንዳንድ ሪስቶራንቶች ለሲጋራ አጫሾች የተለየ የማጨሻ ክፍሎችና ቦታዎች አላቸው።