የጤና እንክብካቤ ኢንሹራንስ (መሰረታዊ ኢንሹራንስ)
ሁሉም የስዊዘርላንድ ነዋሪዎች የጤና መድህን (መሰረታዊ ኢንሹራንስ፣ Grundversicherung) ራሳቸው የግድ መግባት አለባቸው። ወደ ስዊዘርላንድ ለመኖር አገር የሚቀይር ማንኛውም ሰው ይህን ለማድረግ ሦስት ወር አለው። በዚህ ጊዜ ውስጥ አንድ ሰው ቢታመም፣ ቢሆንም እንኳን ይሸፈናሉ። መሰረታዊ ኢንሹራንስ በብዙ የግል የጤና መድን አገልግሎት ሰጪዎች (Krankenkassen) ይሰጣል። የጤና ኢንሹራንስ ኩባንያዎን ለመምረጥ ነፃ ነዎት። የጤና ኢንሹራንስ ኩባንያዎች በስዊዘርላንድ የሚኖሩትን ሁሉ የመቀበል ግዴታ አለባቸው።
ኢንሹራንስ የገባ ሰው በየወሩ መክፈልል የሚገባውን ሂሳብ ይከፍላል። እነዚህ ፕሪሚየሞች እንደ ጤና ኢንሹራንስ ኩባንያ እና እንደ ኢንሹራንስ ሞዴል ይለያያሉ። ስለዚህ ቅናሾቹን ማወዳደር ጠቃሚ ነው። ለሚቀጥለው ዓመት እስከ ህዳር መጨረሻ ድረስ የጤና መድን መቀየር ይችላሉ። መሰረታዊ ኢንሹራንስ ከታመሙ ወጪዎችን ብቻ ሳይሆን በእርግዝና እና ልጅ በመውለድ ጊዜም ጭምር ይከፍላል። የሚሰጡት አገልግሎቶች (ጥቅሞቹ) በሕግ የተደነገጉ ናቸው::
ማሳሰብያ፡ ለጥርስ ህክምና ወይም የመነጽር ወጪዎች አብዛኛውን ጊዜ በራስዎ መከፈል ወይም በፈቃደኝነት ተጨማሪ ኢንሹራንስ መግባት አለብዎት።