ማስጠንቀቂያ እና ዕዳ ማስፈጸሚያ
የሒሳብ ክፍያ በሰዓቱ ካልከፈሉ፣ በመደበኛነት የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ማስጠንቀቂያ (Mahnung). ይደርሰዎታል። ሆኖም አበዳሪዎች በማንኛውም ጊዜ የዕዳ ማስፈጸም (Betreibung) የማስጀመር ስልጣን አላቸው። በዚህ ግዜ ተበዳሪው ከሚመለከተው የዕዳ ማስፈጸሚያ ቢሮ (Betreibungsamt). የክፍያ ትዕዛዝ ይደርሰዋል።. ለአሰራር ሂደቱ ተጨማሪ ያስከፍላል። የዕዳ ማስፈጸሚያው ህጋዊ አይደለም ብሎ የሚያምን ማንኛውም ሰው፣ ህጋዊ ፕሮፖዛል (Rechtsvorschlag) ኃላፊነት ካለው የዕዳ ሰብሳቢ ጽሕፈት ቤት በማቅረብ መቃወም ይችላል። ማሳሰቢያ፡ ዕዳ አስፈጻሚው ደሞዝ ወይም ውድ ዕቃዎችን እንደ መያዣ አድርጎ ሊይዝ ይችላል። በተጨማሪም የዕዳ አስፈጻሚው በዕዳ ማስፈጸሚያ መዝገብ (Betreibungsregister) ውስጥ (ከፍለው እንኳን ቢሆንም) መዝግበው ይይዛሉ።. ከሌሎች ነገሮች በተጨማሪ አፓርታማ በሚፈልጉበት ጊዜ ችግር ሊፈጥርብዎት ይችላል።.