ብዙውን ጊዜ የሒሳብ ክፍያዎች (Rechnungen) በፖስታ ወይም በኢሜይል በመክፍያ ደረሰኝ ዝርዝር ይላካሉ። ሊታሰብባቸው የሚገቡ ሦስት የአከፋፈል አማራጮች አሉ፡-
- ኢ-ባንኪንግ፡ በኢንተርኔት በኩል የሚደረጉ ግብይቶችን ክፍያዎች በጣም የተስፋፋ እና አስተማማኝ ናቸው።
- በባንክ መክፍያ መስኮት፡ በመክፍያ ደረሰኝ በፖስታ ቤት በጥሬ ገንዘብ ክፍያ መክፈል ይቻላል። የፖስታ ባንክ ያለው ሰው ገንዘቡን በቀጥታ ከባንክ ሒሳቡ መክፈልና ማስተላለፍ ይቻላል። የባንክ ደንበኞች ከባንክ ክፍያዎችን በባንክ መክፍያ መስኮት ክፍያውን መፈጸም ይችላሉ።
- በፖስታ፡- ገንዘብን ለማስተላለፍ በፖስታ አድርጎ ለባንክ ወይም ለፖስታ ቤት መላክ ይቻላል። እባክዎ ተጨማሪ መረጃው ለማግኘት ባንክ ቤት ወይም የፖስታ ቤት ባንክ ቤት ይጠይቁ።
ለሚደጋገሙ ሒሳቦች የአከፋፈል አማራጮች፡-
- የቀጥታ ክፍያ ሂደት Load Ledger Vendor (LSV) አላላክ ምቾት ይሰጣል።ምክንያቱም የሒሳብ ክፍያው ወድያውኑ በፍጥነት ከባንክ ሒሳብ ላይ ይወስዳል። ስለ ሁኔታው ተጨማሪ መረጃው ለማግኘት ባንክ ቤት ወይም የፖስታ ባንክ ቤት ይጠይቁ።
- ሂሳቡ ከፍ ያለ ከሆነ (ለምሳሌ ያህል የኪራይ ክፍያ) በባንክ ወይም በፖስታ ባንክ ቤት ገንዘቡ በግዜው ባንኩ እንዲያስተላልፍ ዘለቄታው ውል (Dauerauftrag) መፈጸም ይቻላል።
ክፍያዎች ሁልግዜ የክፍያ የጊዜ ገደብ አላቸው።መጠየቅ ይችላሉ። ይህ የክፍያ የጊዜ ገደብ ክፍያው ሳይፈጸም ገደቡ ቢያልፍ፣ ጣጣ ሊያመጣ ይችላል። ገንዘቡን የግድ ከነቅጣቱ ማስከፈል (Betreibung) ይቻላል።