የስራ ፈቃድ
አብዛኛውን ግዜ የመኖሪያ ፈቃድ ከተሰጠ የስራ ፈቃድ በአንድ ላይ ነው የሚሰጠው፣ ስለዚህ የስራ ፈቃድ ጥያቄ በዚሁ መልስ ያገኛል። በመሰረቱ የመኖር መብት ያላቸው ሰዎች ስዊዘርላንድ ውስጥ ስራ መስራት ይፈቀድላቸዋል። እንደ ዜግነቱ እና የስራው ርዝማኔው ታይቶ ስራ ቀጣሪው ወይም ሰራተኛው የስራ ፈቃድ ያመለክታል። እርግጠኛ ለመሆንና ለማጣራት ከዚህ በታች የተጠቀሱት ቢሮዎች ሊያግዝዎት ይችላሉ። እነዚህ ቢሮዎች በስዊዘርላንድ ውስጥ እስካሁን ላልኖሩ እና እዚህ መስራት ለሚፈልጉ ሰዎች ምክር ይሰጣሉ። እውቅና ያላቸው ስደተኞች (ፈቃድ B) እና ለጊዜው ተቀባይነት ያገኙ የስደተኛ ደረጃ ያላቸው ወይም የሌላቸው (ፈቃድ F) ያላቸው ልዩ ፈቃድ አያስፈልጋቸውም። ይሁን እንጂ የእያንዳንዱ ሥራ መጀመሪያ እና መጨረሻ ጊዜ ኦፊሴላዊ ቅጽ በመጠቀም ለካንቶኑ ሪፖርት መደረግ አለበት። (የምዝገባ ሂደት፣ Meldeverfahren) ። ሪፖርት የሚደረገው በሚሰሩበት ካንቶን ነው። ምዝግባው ነጻ ነው። ጥገኝነት ጠያቂዎች (መታወቂያ N) ያላቸው ፈቃድ ያስፈልጋቸዋል።