ዕውቅና
የውጭ አገር ዲፕሎማ ያላቸው ሰዎች በተወሰኑ ሁኔታዎች በስዊዘርላንድ ውስጥ እውቅና ሊያገኙ ይችላሉ። እውቅናው የውጭ አገር ዲፕሎማው ወይም ዲግሪው ከስዊዘርላንድ ዲፕሎማ ወይም ዲግሪ ጋር እኩል መሆኑን ያረጋግጣል።.ቁጥጥር የሚደረግባቸው ሙያዎች (ለምሳሌ የነርሲንግ ባለሙያዎች፣ መምህራን፣ ወዘተ) ከሆነ በሙያውን ለመስራት የግድ ዕውቅና ያስፈልጋል። ለዕውቅናው እንደ ሙያው ወይም እንደ ትምህርቱ ዓይነት የተለያዩ አካላት እውቅና ይሰጣሉ።ለእውቅናውም ክፍያ ይከፈላል።. የብሔራዊ የዲፕሎማና የዲግሪ ዕውቅና ማዕከል (Nationale Kontaktstelle für Diplomanerkennung) ወይም ከሙያ፣ ጥናትና የሥራ አማካሪ አገልግሎት (Berufs-, Studien- und Laufbahnberatung) መረጃ ማግኘት ይቻላል።